የልደታ ክፍለ ከተማ
መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

በከተማችንን ብሎም በክ/ከተማችን የሚታየውን ድህነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ ለአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል በተለይም ሴቶችንና ወጣቶችን በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት የስራ እድል እየተፈጠረላቸዉ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ የማምረቻ፣ የመሸጫ እና የማሳያ ቦታ አቅርቦት በሚፈለገው ደረጃ እና ፍጥነት ለኢንተርፕራይዞች ማቅረብ አለመቻሉ እንዲሁም ተሰርተው የቀረቡ የመስሪያ ቦታዎች የሚገነቡባቸው ቦታዎች ምቹ አለመሆን፣ የግንባታ ጥራት መጓደልና መጓተት፤ መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው መሆናቸው ከዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት በሚፈለገው ደረጃ ማድረስ አልተቻለም፡፡

ስለሆነም በክፍለ ከተማው የሚታየውን የማምረቻ፣ማሳያ እና መሸጫ ቦታ ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማትን በማሳተፍ አስፈላጊውን ስትራቴጂ በመንደፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ የመስሪያ ቦታ ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት የመስሪያ ቦታዎችን በማልማት እና በማስተዳደር በዘርፉ ያለውን የመስሪያ ቦታዎች ልማት እና አስተዳደር ችግሮች...... ተጨማሪ ያንብቡ

ወ/ሮ ብርቱካን ባህሩ , የልደታ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

ብስራት አያለዉ;
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት አስተባባሪ

የጽ/ቤቱ አስተባባሪ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናዉናል:-
  • የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ለአዲስና ነባር ኢንተርፕራይዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ከአድልዎ ነጻ በሆነ መልኩ በእኩልነትና በፍትሀዊነት ተደራሽ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ ነው።
  • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት ለማስፈን፣
  • አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግ

የጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎች

አቶ ተሾመ አየነዉ

የመስሪያ ቦታ ማደራጀት፣ የማስተላለፍና መረጃ ጥንቅር ቡድን መሪ

አቶ ቴዎድሮስ ደገፋ

የመስሪያ ቦታ ልማት ስራዎች አቅርቦት ቡድን መሪ

አቶ ንጉሴ መብራቱ

የመስሪያ ቦታ ልማት ስራዎች የደንበኞች አገልግሎት ቅሬታ አበቱታ አፈታት ቡድን መሪ

አቶ ረቢራ ሌሎ

የመስሪያ ቦታዎች አካባቢ ሚቹነት ደህንነትና ቁጥጥር ቡድን መሪ

የልደታ ክ/ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡

ጥያቄ ካልዎት እባክዎ ለመደወል አያመንቱ ወይም ይጎብኙን!!

+251923110074

አድራሻችን:-

የልደታ አስተዳደር ህንጻ 3ኛ ወለል ቢሮ ቁ 303
የስራ ሰዓት ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 2፡30 - ቀኑ 11፡30