image
image
image
image
image

የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በልደታ ክፍለከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ምልከታ አካሄደ፡፡

ሰኔ 15, 2018
የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በልደታ ክፍለከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በመገኘት ምልከታ አካሄዷል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር አቶሜ አበበ ክፍለ ከተማው በርካታ በህገወጥ የተያዙ ቤቶችን በማስለቀቅ እና ለሚመለከታቸው በመስጠት ያከናወነው ተግባር ለሌሎች ክፍለከተሞችም አርአያ የሚሆን ሲሆን ከዚህም ሌላ ጽ/ቤቱ የተሻለ አገልግሎት አሰጣጥም የታየበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ጽ/ቤቱ ጠንካራ እና የተሻሉ አሰራሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል ከዚህ በበለጠ አሰራሩን ለማሻሻል መስራት ይጠበቅበታልም ብለዋል፡፡ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች በቴክኖሎጂ የተሻለ አሰራር መኖሩ ፤ በተለያየ ምክንያት ወደ ሲስተም ያልገቡ ቤቶችን ከስር ከስር እያስገቡ መሆኑ ፤ ውል ያልገቡ ቤቶችን ወደ ውል ስርአት ማስገባታቸው እና በሌሎችም ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም ላይ የሚገኝ ነው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ