image
image
image
image
image

በ2018 በጀት ዓመት በ6 ወራት ውስጥ ለ81 ኢንተርፕራይዞችና ለ 187 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ማስተለፉን የልደታ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ገለፀ

የካቲት 10, 2018
ጽ/ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወር አፈፃፀሙን ገምግሞ ውጤታማ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ባለድርሻ አካላት እውቅና ሰጥቷል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱኳን ባህሩ ባደረጉት ንግግር ባለፉት 6 ወራት ለ81 ኢንተርፕራይዞችና ለ187 አንቀሳቃሾች የመስሪ ቦታ አስተላልፈናል ብለው በዚህም ወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ችለናል ሲሉ ገልፀዋል። በ6 ወሩ የመስሪያ ቦታን 5 ዓመትና ከዚያ በላይ ሲጠቀሙ የነበሩ 24 ኢንተርፕራይዞችን የማስለቀቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል ወ/ሮ ብርቱካን ባህሩ። መሰረተ ልማት ዝርጋታን በተመለከተ በ6 ወር 18 የመብራት ቆጣሪ፣ 1 ትራንስፎርመር እና 2 የውሀ ቆጣሪ የማስገባት ተግባር መከናወኑንም ገልፀዋል። በእለቱም ለአረጋዊያን ቤት ያደሱና ማዕድ ላጋሩ ኢንተርፕራይዞች፣ በቅንጅት ስራ ውጤታማ ተሳትፎ ለነበራቸው ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጥቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች