image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በ5ኛ ዙር ለ26 ኢንተርፕራይዞችና 86 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ እጣ አወጣጥ ፕሮግራም አካሄደ።

ሚያዚያ 11, 2018
በእጣ አወጣጥ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱኳን ባህሩ እንደገለፁት መንግስት የስራ አጥነትን ለመቅረፍ ባለዉ ቁርጠኝነት በያዝነዉ በጀት አመት ውስጥ ለ100 ኢንተርፕራይዝና 218 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ያስተላለፍን ሲሆን በዛሬዉ ቀንም ለ26 ኢንተርፕራይዝና 86 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ማስተላለፍ ስራ አከናውነናል ብለዋል። ወ/ሮ ብርቱካን አያይዘዉም የዛሬ እድለኛ የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚዎች ያገኛችሁትን ውስን ሀብት በአግባቡ ተጠቅማችሁ ዉጤታማ በመሆን ከራስ በማለፍ ሀገርና ህዝብን የምትጠቅሙ እንድትሆኑ በጥረትና በትጋት መስራት አለባችሁ ሲሉ አሳስቧል። በማስተላለፍ እና እጣ አወጣጡ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ ክህሎት ምክትል ኃላፊ አቶ ክብሮም ዳኢ ለተጠቃሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት የዛሬ ባለ እድለኞች መስሪያ ቦታን ማግኘት ትልቅ እድል እንደ ሆነ ገልፀዉ ይህን መልካም እድል ተጠቅመዉ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ የበኩላቸዉን ከፍተኛ ሚና እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል። የእጣ አወጣጥና የማስተላለፍ ስነ ስርዓቱ ከተከናወነ በኋላ የእድሉ ተጠቃሚዎችም ስላገኙት እድል መንግስትን በማመስገን የተሻለ ስራ ሰርተዉበት ዉጤታማ እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች