image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ90 ቀናት ዕቅድ ውይይት አካሄደ

ሰኔ 24, 2018
የልደታ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ በ90 ቀናት የታቀዱ ተግባራት ዙሪያ ከአመራሮችና ከሠራተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል። መድረኩን የመሩት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ባህሩ ሲሆኑ በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን፣ የታዩ ጥንካሬዎችን እና መሻሻል የሚገባቸውን ክፍተቶች በዝርዝር አቅርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ የ90 ቀናት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ተሳታፊዎች ገንቢ ሀሳቦችንና አስተያየቶችን በማቅረብ የዕቅዱን ተግባራዊነት ለማጠናከር ቃል ገብተዋል። ወይዘሮ ብርቱካን ባህሩ በማጠቃለያቸው የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከር እና የታዩ ክፍተቶችን በመቅረፍ በቀጣይ ወራት የላቀ ውጤት ለማምጣት ሁሉም ሠራተኞች በቅንጅትና በተጠያቂነት እንዲሠሩ አሳስበዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች