image
image
image
image
image

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወር የተግባር አፈጻፀም ምዘና የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች ዕውቅና ሰጠ።

መጋቢት 12, 2018
በዚህም መሰረት የልደታ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ከ11ዱ ክ/ከተሞች 3ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል። “ዕውቅናው በ11ዱም ክ/ከተሞች መካከል የውድድርና የተነሳሽነት ስሜት በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያግዝ ሲሆን ይህ ውጤት የክ/ከተማው አመራርና ሰራተኞች በጋራና በትጋት የሰሩት ጠንካራ ተግባር መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ለተመዘገበው ስኬት ሁሉንም የጽ/ቤቱ አመራር፣ የስራ አስተባባሪ፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በቀጣይ ቀሪ ስራዎቻችንም የላቀ ውጤት ለማምጣት ከዚህ በበለጠ መስራት ይጠበቅብናል። እንኳን ደስ አላችሁ

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች